Wed02212018

Last updateTue, 24 May 2016 11am

Back You are here: Home

Articles

ምርጫው እየተቃረበ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ከባድ ችግር ውስጥ ወድቋል

 

ዋና ዋና የሚባሉት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም የሚካሄደው አጠቃላይ ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ያላቸው ግንኙነት በብዙ መልኩ ፈተና የበዛበት ሆኗል፡፡ ይህ በምርጫው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ዘንድ ፍትሃዊ የሆነ የመወዳደሪያ ሚዳ ሊፈጥር ባለመቻሉ ምክንያት የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድምጽ የሚሰጥበት ቀን ሲደርስ ራሳቸውን ከውድድሩ ሊያገሉ እንደሚችሉ በይፋ እስከመግለጽ ደርሰዋል፡፡

ታህሳስ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ “በአፍራሽ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ” በሚል ቦርዱን ይቅርታ እንዲጠይቅ ለፓርቲው ደብዳቤ ፅፏል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም በላከው የመልስ ድብዳቤ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን ጥያቄ “ህገ-ወጥ” ነው በሚል ውድቅ ያደረገው ሲሆን ቦርዱ ሆን ብሎ ፓርቲውን ከመወንጀል ስራው እንዲቆጠብም አሳስቧል፡፡  አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲም (መኢአድ) እያንድአንዳቸው አለባቸው የተባለውን የውስጥ ችግር እንዲፈቱ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከቦርዱ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው ቆይቷል፡፡

ሆኖም አንድነት እና መኢአድ ምርጫ ቦርድ በውስጥ ጉዳዮቻቸው ላይ ያለአግባብ ጣልቃ እየገባ መሆኑን ብሎም ከምርጫው ሊያገላቸው እየጣረ እንደሆነ ይከሳሉ፡፡ መኢአድ በተለይ ለሶስተኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ ከምርጫ ቦርድ መጠየቁ አላስደሰተውም፤ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ማሙሸት አማረ “ቦርዱ መኢአድን ከምርጫው ለማድለል ተልኮ አለው” ብለዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አስራት ጣሴም የኢትጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲያቸውን ለማፍረስ ተልኮ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር የፈጠሩት ቅራኔ ቦርዱ በውስጥ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ ይገባል በሚለው ውንጀላ ብቻ የተመሰረተ አይደለም፡፡ የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫን አስመልክተው ፓርቲዎቹ ሳይታዘቡት ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የተካሄደ እና ይሄም ቦርዱ ሆን ብሎ ገዥውን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢህአዴግ) ለመጥቀም ያደረገው ነው ብለዋል፡፡

የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ታህሳስ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ምህረት የተካሄደ ሲሆን ምርጫው ከተካሄደ አንድ ቀን በኋላ ሰማያዊ ፓርቲን እና መኢአድን የሚጨምረው የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሰራር ውስጥ የገዥው ኢህአዴግ ፓርቲ ጣልቃ ገብነት እንዳለ ተናግሯል፡፡ የአራት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ታህሳስ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ እንዲሰረዝ እና በድጋሚ እንዲካሄድ ጠይቋል፡፡ የፓርቲው የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ዶክተር መረራ ጉዲና “የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫን ህዝቡ ወጥቶ ይመርጥ ዘንድ ለህዝቡ በስፋት አልተዋወቀም” ብለዋል፡፡

ይህ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና ዋና ዋና የሚባሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ያለው ውጣ ውረድ የበዛበት ግንኙነት የተወሰኑትን ድምፅ በሚሰጥበት ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ተሳትፍ ስለማድረጋቸው እርግጠኛ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ በሃገር ውስጥ የሚታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው ሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢአድ እና መድረክ የሃገሪቱ የፖለቲካ መጫወቻ ሜዳ እንደጠበበ እንደሚገኝ ገልጸዋል፤ እንዲሁም መንግስት ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ያደርገው ዘንድ ጠይቀዋል፡፡ ይህ ሊሆን ካልቻለ ግን ድምጽ መስጫ ጊዘው በደረሰ ወቅት ራሳቸውን ከምርጫው ሊያገሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሆኖም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለመጭው የግንቦት ወር 2007 ዓ.ም. ምርጫ ስኬት ሁሉም ፓርቲዎች  ተባብረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሃገር ውስጥ የሚገኙ ተቀዋሚ ፓርቲዎችን ሁሌም ህግ እና ስርዓትን አክብረው የሚሰሩ፣ እንድ አንዴ የሚያከብሩ በሌላ ጊዜ ደግሞ የሚጥሱ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ህግ እና ስርዓትን የማያከብሩ በሚል በሶስት ከፍለዋቸዋል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ባለ የመንግስት እና ገዥ ፓርቲ አሰራር በሀገር አስተዳደር ላይ በትክክል ባልተለየበት ሃገር የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቀዋሚ ፓርቲዎችን በዚህ መልኩ ከፋፍሎ ማስቀመጥ እና የተወሰኑትት ላይም የቅጣት እርምጃ እንደሚወስዱ መናገራቸው መንግስት የገዥውን ፓርቲ ዋና ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ በተቀዋሚ ፓርቲዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል የተወሰኑ ፓርቲዎች ሰላይ ስጋት አሳድሯል፡፡  ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲ በምርጫው ሂደት እንዳይሳተፍ ለማድረግ የተለያዩ እንቅፋቶችን ለመጣል የውስጥ ስምምነት ላይ መድረሱን አንድነት ገልጿል፡፡

በተቃራኒው ደግሞ አህአዴግ በፌስቡክ ማሕበራዊ ድረ ገጹ ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም. እንደገለጸው ገዢው ፓርቲ መጪው ምርጫ “ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍርሃዊ፣ ነጻ እና በህዝብ ዘንድ ታዓማኒነት ያለው” እንዲሆን ሚናውን በተግባር እንሚጫወት ገልጿል፡፡ የመንግስት ኮምዩኒኬይሽን ጉዳዮች ቢሮም ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ መንግስት የምርጫው ሂደት “ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና መሁሉም ዘንድ ተዓማኒ እንዲሆን” ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግሯል፡፡ የቢሮው ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እውነቱ ብላታ እንደተናገሩ የዚህ ዓመት ምርጫ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ እንዲሆን ዓለም ዓቀፍ መስፈርት መሰረት ያሟሉ የምርጫ አሰራሮች ተዘርግተዋል ብለዋል፡፡

የሆነ ሆኖ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ተቀዋሚ ፓርቲዎች እና ገዢው ፓርቲ መካከል ያለው እሰጥአገባ በለተይ ምርጫው እየተቃረበ በሚመጣበት ጊዜ የበለጠ እየተካረረ እንደሚሄድ ይጠበቃል፡፡