Wed02212018

Last updateTue, 24 May 2016 11am

Back You are here: Home የምርጫ ዜናዎች ኢትዮጵያ፤ ተቃዋሚዎች በአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሀን ሽፋን እጥረት ያጋጠማቸው ፈተና

ኢትዮጵያ፤ ተቃዋሚዎች በአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሀን ሽፋን እጥረት ያጋጠማቸው ፈተና

የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን በመንግስት ተጽእኖ ስር በማረፉ ሳቢያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀጣዩን ምርጫ የሚመለከቱ መልእክቶቻቸውን ለህብረተሰቡ ለማድረስ ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ላይ መሆናቸውን ይገልጻሉ።

አስቸጋሪ ሁኔታ ነው የገጠመንይላሉ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ አስራት አብርሀም። በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ያለው የሚዲያ ሁኔታ ከየትኛውም ወቅት በከፋ መልኩ ፍጹም ዝግለተቃዋሚዎች ፈጽሞ የማይመች ነውአብዛኞቹ የግል ሚዲያዎች የተዘጉበትጋዜጠኞች በብዛት የተሰደዱበትና በከፊል ደግሞ በእስርቤት የታጎሩበት ሁኔታ ነው ያለው።

በተመሳሳይ መልኩ የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የጉዳዩን አሳሳቢነት እንዲህ ሲሉ ይገልጻሉ፤ ይህ በእውነቱ ታስቦበት የተደረገ ነው። ከቀደምት ምርጫዎች አንጻር በተለይም 1997 .በኋላ እንኳን ምርጫ ኖሮ ይቅርና በማቸውም ሰዓትም ሚዲያዎች እጅግ ፈኑና ያሉትም ወይ ለገዢው የሚያገለግሉ አልያም በፍርሃት ድባብ ያሉ ናቸው፡፡ ከዛ የተረፉት ደግሞ ህትመታቸው እጅግ አነስተኛ ነው ከወራት በፊት በጅምላ የተከሰሱ የህትመት ሚዲያዎችም ምርጫውን ተከትሎ የተወሰደባቸው እርምጃ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ ብቸኛ የሆነውን ብሄራዊ የቴለቪዥን ጣቢያና ለብዙሀን ተደራሽ የሆነውን የሬድዮ ጣቢያ መንግስት በብቸኝነት ይቆጣጠረዋል። በክልሎች የሚገኙ የመገናኛ ብዙሀንም ቢሆኑ እንዲሁ በክልል መንግስታት ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆኑ፤ ኤፍ ኤም ጣቢያዎችም እንዲሁ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ገዢው ፓርቲ የሚዘውራቸው ቸው።

 

እናስ ተቃዋሚዎች የቀራቸው አማራጭ ምን ይሆን?

መገናኛ ብዙሀኑ በገዢው ፓርቲ ተጽእኖ ስር በመውደቃቸው የተነሳ ፓርቲያችን በማበራዊ ድረገጽ ላይ በንቃት ተሳትፎ በማድረግ የአግድም መረጃ ልውውጡን ይጠቀምበታልበማለት አቶ ዮናታን ስላላቸው አማራጮች ያወሳሉ።በአገዛዙ ጫና ከህትመት የወጣችው የፓርቲው ልሳን ነገረ-ኢትዮጵያም በዚሁድረ-ገጽ በኩል መረጃ እናሰራጫለን።

ምንም እንኳ የህትመት ቁጥሩ በሳምንት ከሁለት ሺህ ባይዘልም አንድነት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው በሀገሪቱ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱት ፓርቲዎች መካከል (ደጋፊ ከሚባሉት ውጭ) ፍኖተ ነጻነት የተሰኘ የራሱን ጋዜጣ ያሰራጫል።

አቶ አስራት እንደሚሉት ፓርቲያቸው የራሱን ማተሚያ ቤት ለማቋቋም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ከመሆኑም ባሻገር ከሁለት አመት በፊት መንግስት በሚቆጣጠረው ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት እንዳትታተም ተደርጋ ከገበያ ውጪ የሆነችውን ጋዜጣቸውን በቅርቡ ወደ አንባቢዎቿ ተመልሳለች።

መልእክታችንን ወደ ህዝቡ ለማድረስ ማህበራዊ ድህረገጾችን ጨምሮ ማናቸውንም አማራጮች እንጠቀማለንብለዋል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሚገለገሉባቸው ሌሎች አማራጮች መካከል በአጭር ሞገድ የሚሰራጩት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮና የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ናቸው። መንግስት እነዚህን ሁለት ጣቢያዎች 2002 ምርጫ ወቅት አግዷቸዋል የሚል ክስ ቀርቦበት የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ሌላውና ዋንኛው ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚገለገሉበት የመገናኛ ብዙሀን ደግሞ ሀያ አራት ሰአት በቀጥታ ከአምስተርዳም፣ ለንደንና ዋሽንግተን ስቱዲዮዎች በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራጨው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዝን (ኢሳት) ነው።

2002 .ስርጭቱን የጀመረው ይሄው ጣቢያ የኢትዮጵያ መንግስት ስርጭቱን በአግባቡ እንዳያካሂድ እገዳ እያደረገበት መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል። መንግስት በበኩሉሽብርተኛሲል የፈረጀውን ግንቦት ሰባት አገልጋይ ነው ሲል ጣቢያውን ይወነጅላል።

ይሁንና ነጻ የሆነ የመገናኛ ብዙሀን እንዲሁም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሀገሪቱ ውስጥ ሊከበር ይገባዋል በማለት የሁለቱም ፓርቲ መሪዎች በአጽንኦት ይናገራሉ።

ያለዚያ የህዝቡን መብት የሚያከብር ዴሞክራሲያዊ መንግስት መፍጠር አስቸጋር ይሆናል። በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትና አለማቀፉ ህብረተሰብ መንግስት እነዚህን መብቶች እንዲያከብር አስፈላጊውን ሁሉ ጫና ሊያደርጉ ይገባልብለዋል።