Sat02172018

Last updateTue, 24 May 2016 11am

Back You are here: Home የምርጫ ዜናዎች ለፓርቲዎች በተሰጠው የመገናኛ ብዙሀን ክፍፍል ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግየ አንበሳውን ድርሻ ወስጿል!

ለፓርቲዎች በተሰጠው የመገናኛ ብዙሀን ክፍፍል ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግየ አንበሳውን ድርሻ ወስጿል!

በቀጣዩ ምርጫ ለሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብሄራዊና ክልላዊ የመንግስት የመገናኛ ብዙሁን ሽፋን ማከፋፈሉን የምርጫ ቦርድ አስታውቆዋል። በዚህም መሰረት ከተከፋፈለው የሬድዮና የቴለቪዝን የአየር ሰአት እንዲሁም የጋዜጣ ገጾች ኢሀአዴግ ከፍተኛውን ድርሻ አግኝቷል። በቦርዱ ገለጻ መሰረት በህዝብ ተወካዮች እና በክልል ምክር ቤት መቀመጫ ላላቸው 40 ፐርሰንት፣ ዕጩ ላቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች 40 ፐርሰንት፣ የሴት ዕጩ ላቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች 10 ፐርሰንት፣ በእኩልነት መስፈርት 10 ፐርሰንት እንዲሆን ቦርዱ ወስኗል፡፡ በብሄራዊ ደረጃ የሚነቀሳቀሱ ፓርቲዎች ብሄራዊ የመገናኛ ብዙሀንን የሚገለገሉ ሲሆን በክልል የሚንቀሳቀሱት ደግሞ ክልላዊ የመገናኛ ብዙሀንን ይጠቀማሉ። በ 2002 አ. ም. በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በህዝብ ተወካዮች እና በክልል ምክር ቤት ወንበር ላላቸው 55 ፐርሰንት፣ ዕጩ ላቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች 20 ፐርሰንት፣ በእኩልነት መስፈርት 25 ፐርሰንት ተደልድሎ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳ የዚህ አመት ድልድሉ ከባለፈው ምርጫ ጋር ሲነጻጸር የተሻለና የሴቶችንም ተሳትፎ ያካተተ ቢሆንም አሁንም ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ፍትሀዊነት የታየበት አይደለም። ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ በምርጫ ወራት መገናኛ ብዙሀን የፖለቲካ ፓርቲዎችን መረጃ ወደ ህዝቡ ለማድረስ ያላቸው ጠቀሜታ እጀግ ከፍ ያለ ነው። ውይይቶችንና ክርክሮችን በማመቻቸት፣ ስለ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችና እጩ እንደራሴዎች አስፈላጊውን መረጃ ሁሉ ወደ ህዝቡ በማድረስ የመገናኛ ብዙሀን መራጩ በራሱ በራሱ እንዲተማመን ያስችላሉ። ዜጎች በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ እንዲሰጡ ለማድረግ መገናኛ ብዙሀን ያላቸው ሚና እጅግ የጎላ ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ የህዝብ የሚዲያ ተቋማት ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በራቸውን እኩል ሊከፍቱላቸው ይገባል። የአንድ ሀገር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማሳያ ከሁኑት መካከል አንዱና ዋነኛው የተለያዩ ሀሳቦችን በእኩል ሁኔታ ለማንሸራሸር የሚረዳ የህዝብ መገናኛ ብዙሀን መኖር ነው። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሚዲያ ድልድል ለምን ተቀባይነት አጣ? የድልድሉን መሰረታዊ ስሌት ለተመለከተው ምን ያህል ከመነሻው ወገንተኝነት የሚታይበት እንደሆነ ለመረዳት የሚከብድ አይሆንም። ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከአንድ በስተቀር የፓርላማ መቀመጫዎችን በሙሉ የተቆጣጠረ ሲሆን የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎችንም እንዲሁ ሙሉ ሉበሙሉ ይዟቸዋል። ይህ ማለት ደግሞ በድልድል ስሌት ውስጥ ከተቀመጠው 40 ፐርሰንት የመገናኛ ብዙሀን ሽፋን ሙሉውን ለብቻው እንዲጠቀም ያስችለዋል። ከዚህ በተጨማሪ እጩ ላቀረቡ ፓርቲዎች ተብሎ በተቀመጠው 40 ፐርሰንት እንዲሁ ኢህአዴግ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል። ይህም የሚሆንበት ምክኒያት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የኢህ አዴግን ያህል የሰው ሀይልም ሆነ የበጀት አቅም ስለማይኖራቸው ቁጥሩ ከፍ ያለ እጩ ተወዳዳሪ ሊያቀርቡ ስለ ማይችሉ ነው። ዴሞክራሲያቸው እያደገ ባሉ ሀገራት መገናኛ ብዙሀን የምርጫ መረጃ ምንጭ ሆነው ያገለግላሉ። ስለ ተመራጩ ማንነት፣ ሊተገብረው ስላቀደው ፖሊሲና የተለያዩ ህዝባዊ ክርክሮችን ከማመቻቸታቸው ባሻገር ስለ ምርጫው ሂደት፣ የህዝብ አመለካከት፣ የመራጩ ህዝብ መብትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን እየተከታተሉ ይዘግባሉ። ምርጫውን በአንክሮ ይታዘባሉ። ይህ ደግሞ ግቡን ሊመታ የሚችለው ፓርቲዎችም ሆኑ እጩ እንደራሴዎች ሀሳባቸውንና መልእክታቸውን በቀጥታ የሚያቀርቡበት ነጻና ገለልተኛ የመገናኛ ተቋም ሲኖር ነው። እንደ ኢትዮጵያ ባለ ምንም አይነት አማራጭ ሚዲያ በሌለበት፣ የኢትዮጵያ ቴለቪዥንና ራዲዮ አብዛኛውን መራጭ ለመድረስ ብቸኛው አማራጭ በሆነበት አገር ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እኩል እድል መስጠት በምንም መልኩ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ መራጩ ህዝብ ስለሚመርጣቸው ፓርቲዎች ወይም እጩ እንደራሴዎች ሚዛናዊና በቂ የሆነ ግንዛቤ አለው ለማለት አያስደፈርም። ከሁሉም ይልቅ ደግሞ መራጩ ህዝብ ባልተሟላ መረጃ በሚመርጠውና ነገ መንግስት በሚመሰርተው አካል ላይ ፍጹም የሆነ እምነት ይኖረዋል ብሎ ለመናገር አዳጋች ይሆናል።